የፕሪሚየር ሊጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ ምሽት ቀጥሎ ሲካሄድ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
አመሻሽ 11 ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ወደ ጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም አምርቶ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል።
እንዲሁም በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የሚመራው ማንቼስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ቦርንማውዝን ያስተናግዳል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፉልሃም ከሳውዝሃምፕተን እንዲሁም ሌስተር ሲቲ ከዎልቭስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን ቶተንሃም ሆትስፐር ከፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጋር ይገናኛል፡፡