ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ከሚያደርጉልን ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የተገኙ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ከሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ወዳጅነት በጠንካራ የልማት ትብብር ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተገኘውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እና ትብብር ከሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት በማለት ገልጸዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣትም ይህ ዲፕሎማሲያዊ ትብብራችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንድ ማሳያ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የፈረንሳይ መንግስት በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያን እና በብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ በመምጣቶ ክብር ይሰማናል በማለት ጠቅሰው፤ አዲሲቷን ኢትዮጵያን እንደ አዲስ ስለጎበኟትም እናመሰግናለን ብለዋል።