Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረክ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በምክክር መድረኩ የተመረጡ የህብረተሰብ ወኪሎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የመንግስት ተወካዮች ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የማህበራትና ልዩ ልዩ ተቋማት ወኪሎች እየተሳተፋ ይገኛል።

ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ቀደም ሲል ከ356 የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ወኪሎች የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን በማካተት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚቀርቡ ዋና ዋና አጀንዳዎች የሚያደራጁበት ይሆናል ተብሏል።

በዚህ መድረክ ከ1 ሺህ 700 በላይ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች እየተሳተፉ ሲሆን በዚህ ምክክር ምዕራፍ በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ነገር ግን በቅርቡ ከመንግስት ጋር ስምምነት ፈፅመው የተመለሱም ታጣቂዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.