በሰሜን ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ህዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ እና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች ህዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ።
የሰልፉ ተሳታፊዎች ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጠይቀዋል።
ሰላምን ለማረጋገጥ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ መግባታቸውን በማድነቅ፤ በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም የቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ካምፕ መግባት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በሰልፎቹ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል።
በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ካምፕ እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል።