Fana: At a Speed of Life!

የ90 ዓመቷ የፓርኪንሰን ህመምተኛ በክብደት ማንሳት ውድድር ላይ መሳተፍ …

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ነዋሪነታቸው በታይዋን ቴይፓይ የሆነው የ90 ዓመቷ የፓርኪንሰን ህመምተኛ የክብደት ማንሳት ውድድር ላይ መሳተፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

አዛውንቷ ቼንግ ቼን እድሜ ይዞት የሚመጣውን የጉልበት መድከምና የፓርኪንሰን ህመም የሚያስከትለው ከፍተኛ ህመምና ጉዳት ሳይበግራቸው የክብደት ማንሳትን ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሻግረው ለውድድር ያስቡታል ብሎ የገመተ አልነበረም፡፡

በሦስት ዙር ውድድርም 35፣ 40 እና 45 ኪሎ ግራም ክብደት በማሳትም ተወዳድረዋል ነው የተባለው፡፡

ቼንግ ቼን ሁሉም በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ቢያንስ ጤናችሁን እንድትጠብቁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን ብትቀላቀሉ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የውድድሩ አዘጋጆች፥ የውድድሩ ዓላማ የቴይፓይ በዕድሜ የገፉ ማህበረሰብን ማገዝ ነው ብለዋል፡፡

ታይዋን በእድሜ የገፉ ማህበረሰብ ያላት በመባል የምትታወቅ ስትሆን፥ ስያሜው ቢያንስ 21 በመቶው ህዝብ እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ እንደሆነም ይነገራል፡፡

ታይዋን በመጪው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት 288 የአረጋውያን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ክበቦች ለማቋቋም ማቀዷ መገለጹን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.