በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ የደረሠኝ አጠቃቀም ሊተገበር ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘመናዊ አዲስ የደረሠኝ አጠቃቀም ከየካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወንድማገኝ ደግፌ አስታወቁ፡፡
ሕገ-ወጥ ደረሠኝ ጥቂቶችን በመጥቀም የመንግሥትን ገቢ እያሳጣ መሆኑን ያነሱት አቶ ወንድማገኝ÷ በዚህ መነሻ ዘመናዊ የደረሠኝ አጠቃቀምን ለመትግበር በየደረጃው ለሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
የተሻሻለው የደረሠኝ አጠቃቀምም በኦንላይን ደረሠኝ መጠቀምን ጨምሮ የደረሠኝ ፈቃድ አሰጣጥን ያካተተ ዘመናዊ አሠራር መሆኑን እና ከመጪው የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
በማቱሳላ ማቴዎስ