Fana: At a Speed of Life!

ያለምንም ዘመናዊ ትምህርት 6 ቋንቋዎችን አቀላጥፋ የምትናገረው ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) ምንም አይነት ዘመናዊ ትምህርት ሳትቀስም ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፋ የምትናገረው ፓኪስታናዊ ታዳጊ የማህበራዊ ሚዲያን ቀልብ ስባለች፡፡

ሹማሊያ የተባለችው ይህቺ ፓኪስታናዊት ታዳጊ በሂንዱ ኩሽ ተራሮች ዲር እና ቺትራልን በሚያገናኘው አስደናቂ መንገድ ላይ ለውዝ፣ሱፍና መሰል ምግቦችን በመሸጥ ነው ኑሮዋን የምትገፋው፡፡

ይህቺ ታዳጊ ከደምበኞቿ ጋር በምታደርገው ተግባቦት እንግሊዝኛ፣ሳራይኪ፣ ፑንጃቢ፣ ፓሽቶ እና ቺትራሊ ቋንቋዎችን አቀላጥፋ እንደምትናገር ነው የተነገረው፡፡

የዚህች ታዳጊ የቋንቋ ችሎታና በተለይ ደግሞ እንግሊዝኛ ስታዎራ በሙሉ ራስ መተማመንና በፈገግታ ታጅባ መሆኑ አግራሞትን ያጭራል፡፡

ሹማሊያን በማህበራዊ ሚዲያው አነጋጋሪ እንድትሆን ያደረጋት አንድ ታዋቂ ዩቲዩበር ከታዳጊዋ ጋር ሲተዋወቅ በአስገራሚ እንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዋ ተገርሞ ንግግራቸውን በቪዲዮ በማስቀረቱና በኢንስታግራም አካውንቱ በማጋራቱ መሆኑን ኤን ዲ ቲቪ ዘግቧል ፡፡

ታዳጊዋ እንዴት እነዚህን ሁሉ ቋንቋዎች ልታውቅ እንደቻለች ስትገልጽም “አባቴ 14 ቋንቋዎች ይናገር ነበር ፤እኔም ምንም እንኳ ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት የመግባት እድል ባይኖረኝም አባቴ ቤት ውስጥ ስላስተማረኝ ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፌ እናገራለሁ” ስትል በፈገግታ መልሳለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.