Fana: At a Speed of Life!

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚጠይቅ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ።

በህዝባዊ ሰልፉ ከክልሉ መንግስት ጋር ስምምነት በመፈጸም ሰላም እንዲሰፍን ቁርጠኝነታቸው ላሳዩ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራሮች ምስጋና ቀርቧል።

በጫካ የሚገኙ የኦነግ ታጣቂዎችም ለመንግስት የሰላም ጥሪ ምላሽ በመስጠት ወደ ካምፕ በመግባት ሰላማዊ አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ ተላልፏል።

ህዝብ በሰላም እጦት በዘርፍ ብዙ ችግሮች ውስጥ መሆኑን መልዕክት ያስተላለፉት ሰልፈኞቹ፤ በጫካ የቀሩ ታጣቂዎች የህዝብንና የመንግስትን ጥሪ በማክበር በሰላም እንዲገቡ አስገንዝበዋል፡፡

‘ለኦሮሞ ህዝብ መታገል የማህበረሰቡን ፍላጎት ማሟላት ነው፤ ጠመንጃ መፍትሄ አያመጣም ይልቁን ልዩነቶች በምክክር መፍታት ይኖርባቸዋል’ የሚሉ እና ሌሎች ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚጠይቁ መፈክሮችም በህዝባዊ ሰልፉ ላይ ተላልፈዋል።

በሰልፉ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.