Fana: At a Speed of Life!

ቡካዮ ሳካ ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የአርሴናል ክንፍ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጿል፡፡

ተጫዋቹ አርሴናል ክርስታል ፓላስን 5 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በሰጠው መግለጫ ÷ ቡካዮ ሳካን ያጋጠመው ጉዳት ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚያርቀው ተናግሯል፡፡

ይሁን እንጂ ቡካዮ ሳካ ከውድድር ዓመቱ መጠናቀቅ በፊት ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ያላቸው ተስፋ ገልጸዋል፡፡

ቡካዮ ሳካ አነስተኛ የጉዳት ታሪክ ካላቸው የአርሴናል ተጫዋቾች ግንባር ቀደም ሲሆን÷ ቡድኑ ባለፉት ዓመታት ላስዘገበው ስኬት የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.