Fana: At a Speed of Life!

አይ ኤም ኤፍ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መቼ ሊቋጭ እንደሚችል ትንበያውን አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) የሩሲያ – ዩክሬን ጦርነት መቼ እንደሚቋጭ እና እርቅ እንደሚወርድ መተንበዩ ተሰምቷል፡፡

በትንበያ መሰረትም ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2025 መጨረሻ እና 2026 አጋማሽ ላይ ሰላም ያወርዳሉ ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት የዩክሬን ኢኮኖሚ “የተረጋጋ” መሆኑን ያስታወቀው አይ ኤም ኤፍ÷ ሀገሪቱን ለመደገፍ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማጽደቁ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ዩክሬን ኢኮኖሚዋ ከሚጠበቀው በላይ የኃይል ችግርን የመቋቋም አቅም ቢያሳይም፥ በቀጣዩ ዓመት በዚህ ጥንካሬው ላይቀጥል ይችላል ነው ያለው፡፡

ለዚህም በየጊዜው እየጠበበ የመጣው የሥራ ሁኔታ፣ በዩክሬን የኃይል መሠረተ-ልማት ላይ የሩሲያ ጥቃቶች ያደረሱት ተጽዕኖን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችን በምክንያትነት መጥቀሱን አርቲ ዘግቧል፡፡

አይ ኤም ኤፍ የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ሊገባ ጥቂት ቀናት በቀሩት 2025 የሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት በ2 ነጥ5 እና በ3 ነጥብ 5 በመቶ መካከል እንደሚሆን መተምበዩ ይታወሳል፡፡

እንዲሁም እስከ ፈረንጆቹ 2026 ድረስ የሀገር ውስጥ ምርቷ ለማገገም አዝጋሚ እንደሚሆን፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ከ20 በመቶ በላይ የሆነ የፊስካል ጉድለትን ጨምሮ የኢኮኖሚ ችግሮች እንደሚገጥሟትም ተተንብዮአል፡፡

ከ2022 ጀምሮም እስካሁን ኪዬቭ ከምዕራቡ ዓለም 238 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ማግኘቷ የተገለጸ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ የተባለውን 95 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የለገሰችው አሜሪካ መሆኗ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.