አምባሳደር ምስጋኑ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ÷የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዎቹ፤ ይህን ግንኙነት ለማጠናከር ስለመምከራቸው መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡