Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ አየር መንገድ በረራዎች እንዲቆሙ ተደርገው እንደነበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በቴክኒክ ችግር ምክንያት የአሜሪካ አየር መንገድ በረራዎች በመላው ሀገሪቱ እንዲቆሙ ተደርገው እንደነበር ተገለጸ።

ለአንድ ሰዓት ገደማ የቆየው እገዳ አሁን ላይ የተነሳ ሲሆን÷ አየር መንገዱ ችግሩን በተቻለ መጠን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቆ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

በረራዎች በሚበዙበት በገና ዋዜማ ወቅት የአሜሪካ አየር መንገድ በረራዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲቆሙ መደረጋቸው በሺዎች በሚቆጠሩ የበዓል ተጓዦች ላይ መጉላላት አስከትሏል።

የሀገሪቱ አቪዬሽን አስተዳደር ሁሉም በረራዎች እንዳይደረጉ ሲያሳውቅ ስለገጠመው የቴክኒክ ችግር በዝርዝር ያሳወቀው ነገር እንዳልነበር ሮይተርስ ዘግቧል።

ይህ ወቅት ከገና በዓል ጋር በተያያዘ የአሜሪካ አየር መንገድ በሚሊየን የሚቆጠሩ ደንበኞችን የሚያስተናግድበት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.