የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎ(ዶ/ር)ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡