ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ራምታን ላማምራ ጋር ተወያይተዋል ፡፡
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በውይይቱ ÷ ለሱዳን ሰላም ለማምጣት በተለያዩ ወገኖች የተጀመሩ ጥረቶችን አሰባስቦ ወደ አንድ ውጤታማ አቅጣጫ መምራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ራምታን ላማምራ በበኩላቸው ÷በሱዳን ያለው ግጭት የፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም ሰላም እንዲሰፍን መሥራት እጅግ አስፈላጊ ስለ መሆኑ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላም ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደምታደርግ እና ጉልህ ሚና እንዳላትም በውይይቱ መነሳቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡