Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴርና ቤተ-ክርስቲያኗ በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በውይይቱ÷ ቤተ-ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ በሰላም ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋትና በመቀራረብ እንደምትሰራ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው ÷ ቤተ-ክርስቲያኗ አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ፣እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ ሀገራዊ የሰላም ፀሎት እና ጥሪ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግስት በኩል እንደሚከፈል የገለፁት ሚኒስትሩ የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብርና በመደጋገፍ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.