ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የፈረንጆቹን የገና በዓል ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላው ዓለም የፈረንጆቹን የገና በዓል ለሚያከብሩ ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
በመልዕክታቸውም ለኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት እና ለአጠቃላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በዓሉ በሰላም፣ በጤና እና በአብሮነት የተሞላ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡