Fana: At a Speed of Life!

የስኳር ፋብሪካዎች ከክረምት ጥገና በኋላ ማምረት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስኳር ፋብሪካዎች ከ2016 የክረምት ወራት አጠቃላይ የጥገና ሥራ በኋላ መደበኛ የማምረት ሥራ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡

ከጥገና በኋላ ወደ ምርት የተመለሱትም÷ የወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 እንዲሁም ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች መሆናቸውን የግሩፑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፋብሪካዎቹ በክረምቱ ወራት የተለያዩ የእርሻና የመስኖ ማሽነሪዎች እንዲሁም የመስኖ አውታር አጠቃላይ የጥገና ሥራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል ተብሏል፡፡

ወደ ሥራ መመለሳቸውን ተከትሎም ከ300 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳር ማምረት መቻላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በበጀት ዓመቱ ለስኳር ፋብሪካዎች የውጭ ሀገር መለዋወጫ ግዢ 27 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መመደቡ እና እስከ አሁን 10 ሚሊየን ዶላር የመለዋወጫ ግዢ መከናወኑም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.