Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚና ኢጋድ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ እና የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር)  ወክለው በኢትዮጵያ የኢጋድ ተጠሪ አበባው ቢሆነኝ ፈርመውታል።

ስምምነቱ በዋናነት በአመራር ልማት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

የትብብር መስኮቹ ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ ወደ ትግበራው ይገባል ተብሏል።

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.