Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጥረቷን ትቀጥላለች- ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በሱዳን ያለው ግጭት ረግቦ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሱዳን መልዕክተኛ ከሆኑት ራምታ ላማምራ ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ በቀጣናዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሱዳን ያለው ግጭት ረግቦ ሰላም ሊሰፍን በሚገባበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ፕሬዚዳንት ታዬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ለዚህም ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ትኩረት የምትሰጠው ኢትዮጵያ÷ በሱዳን ላለው ግጭትም ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ የምታደርገው ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ራምታ ላማምራ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት መገንዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.