Fana: At a Speed of Life!

ከለውጡ በኋላ ከ37 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች ተላልፈዋል- ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከለውጡ በኋላ ከ37 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለአቅመ ደካሞች መተላለፋቸውን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

በመሠረተ-ልማትና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለነዋሪዎች ምቹ የሆኑ የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውን ያነሱት ከንቲባዋ÷ የከተማዋ ገቢ እንዲጨምርና ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል መደረጉን አንስተዋል፡፡

ሰው ተኮር ተግባራትን ጨምሮ የትምህርት ቤት ምገባ ማዕከላት ማስፋፋት እና የወጣቶችና ሕጻናት ማዘውተሪያ ማዕከላት በመገንባት ስኬቶች መገኘታቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የነዋሪዎችን የቤት ፍላጎት ለመመለስም ከ265 ሺህ በላይ ቤቶች መገንባታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በመዲናዋ የአረንጓዴ ልማት፣ የኮሪደር ልማት፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአንድነት እና የወዳጅነት ዐደባባይ ፓርኮችን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶችም መገንባታቸውን አንስተዋል።

በቀጣይም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዝ አገልግሎት አሰጣጥን ማጠናከር እንዲሁም የመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.