Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ በፊት እንዲጠናቀቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ አሳሰቡ።

የብሔራዊ ስታዲየም የግንባታ ሂደት አፈፃፀም ሪፖርት ዛሬ ተገምግሟል፡፡

በግምገማው ላይም አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የስታዲየሙ አሁናዊ ግንባታ ሁኔታም መጎብኘቱን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ሚኒስትር ዓለምፀሐይ በዚሁ ወቅት ብሔራዊ ስታዲየሙ ከተያዘለት ጊዜ በፊት መጠናቀቅ እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ተቋራጩ በበኩሉ ለስታዲየሙ ቀሪ ሥራዎች የሚሆኑ ግብዓቶችን እያስገባ መሆኑን እና የፕሮጀክቱን አፈጻጸም ለማፋጠን እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.