አዘርባጃን ብሔራዊ ሐዘን አወጀች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዘርባጃን በትናትናው ዕለት በካዛኪስታን በተፈጠረ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ብሔራዊ ሐዘን ማወጇ ተነገረ፡፡
የአዘርባጃን 62 መንገደኞችንና አምስት ሰራተኞችን የጫነ አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ይታወቃል፡፡
ኢምብሬር 190 የተባለው የበረራ ቁጥር ጄ2-8243 የአዘርባጃን አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በሩሲያ ቺቺኒያ ከባኩ ወደ ግሮዝኒ ሲበር እንደነበርም ተገልጿል፡፡
ሆኖም በግሮዝኒ ጭጋግ ምክንያት ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞር የተደረገ ሲሆን፥ ቢያንስ በህይዎት የተረፉ ቢኖሩም ብዙዎችን ለህልፈት የዳረገ አደጋ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም አዘርባጃን የሐዘን ቀን ማወጇን የዘገበው ዥኑዋ ነው፡፡