በአማራ ክልል 377 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለማካሄድ ታቅዷል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክል 377 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ለማከናወን መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረት ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ለዘንድሮው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡
በዚህ መሰረትም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ዜጎች በአፈርና ጥበቃ ሥራው በንቃት እንዲሳተፉ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡
ለአፈርና ጥበቃ ሥራው 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በዚህም 377 ሺህ ሔክታር መሬት ለማልማት ታቅዷል ብለዋል፡፡
ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የሚውሉ አራት ሚሊየን በላይ የቁፋሮ እና ሌሎች መሳሪያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፤ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራ የሚከናወንባቸው 987 ተፋሰሶች መለየታቸውን አቶ እስመላለም ጠቁመዋል፡፡
በመጪው ጥር ወር አጋማሽ አካባቢ በሚጀምረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ማሕበረሰቡ በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ