Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የበዓል ሰሞን (ቦክሲንግ ደይ) መርሐ ግብር 8 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

በዕለቱ ቀደም ብሎ 9፡30 ላይ በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ደግሞ በርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ፣ ቼልሲ ከፉልሃም፣ ኒውካስትል ከአስቶን ቪላ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከቶተንሃም እንዲሁም ሳውዝሃምፕተን ከዌስትሃም በተመሳሳይ ሰዓት ይጋጠማሉ።

በዕለቱ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች ውስጥ ዎልቭስ በሜዳው ማንቼስተር ዩናይትድን ምሽት 2፡30 ያስተናግዳል።

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል በሜዳው በሩድ ቫልኒስትሮይ የሚሰለጥነውን ሌስተር ሲቲ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይገጥማል።

በሌላ በኩል ነገ ሁለት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን÷ ብራይተን ከብሬንትፎርድ 4፡30 ላይ እንዲሁም አርሰናል ከኢፕስዊች ታውን 5፡15 ላይ ይጫወታሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.