Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ ለነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ለነገሌ ቦረና ጠቅላላ ሆስፒታል 20 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተገኘው በኢጋድ ዋና ፀሐፊ በወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) አማካኝነት ሂውማን ብሪጅ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደሆነም ተመላክቷል።

በድጋፍ መርሐ-ግብሩ ላይ የኢጋድ የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ አበባው ቢሆነኝ፣ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱርቃድር ገልገሎ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ቦኮና ጉታ እንዲሁም የምስራቅ ቦረና ዞን የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ድጋፉ የሆስፒታል አልጋዎች፣ የአካል መደገፊያ መሳሪያዎች፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ይገኙበታል።

ድጋፉ የሆስፒታሉን አገልግሎት የሚያሳድግ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፥ ሆስፒታሉ በምሥራቅ ቦረናና አካባቢው ለሚገኙ 100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.