Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 163 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ጀምሮ በአማራ ክልል 163 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 940 አልሚዎች ፈቃድ መሰጠቱን የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ፈቃድ የተሰጣቸው አልሚዎች 20 ሺህ 368 የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ቢሮው ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
አልሚዎቹ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ኬሚካል፣ ኮንስትራክሽን፣ እንጨትና ብረታብረት፣ ቱሪዝም፣ አበባ ልማት፣ ግብርና እና ሪልስቴትን ጨምሮ በሌሎች መስኮች እንደሚሰማሩ ቢሮው አብራርቷል፡፡
በክልሉ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የኢኮኖሚ ድርሻም 8 ነጥብ 5 መሆኑን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡
የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ62 ቢሊየን ብር ጭማሪ ማሳየቱም ተጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል 62 አዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት መግባታቸውን እና ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ49 ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.