ቢሮው እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ያለታሪፍ ጭማሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ አሳሰበ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በመደበኛው ታሪፍ መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማዋ ትራንስፖርት ሮቢ አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ አስተዳደሩ ካቢኔ መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በውሳኔው መሠረት አውቶቡሶች፣ ሚድ ባስ እና ሚኒ ባሶች መደበኛ በሚሰሩበት መስመርና ቀን ላይ በሚከፈለው ሕጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ቢሮው አሳቧል፡፡
ስለሆነም የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታችሁ አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ሲል ጥሪ ቀርቧል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለበለጠ መረጃና ለትራንስፖርት ጉዳይ ጥቆማ ለመስጠት በነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ላይ መደወል እንደሚቻልም ቢሮው አስታውቋል፡፡