Fana: At a Speed of Life!

የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ በጎ ፍቃደኞች የላቀ አስተዋፅዖ ያበረክታሉ – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ በጎ ፍቃደኞች የላቀ አስተዋፅዖ ያበረክታሉ ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለበጎ ፍቃደኛ አገልግሎት ሰጪዎች እና ለዲፕሎማቶች ላለፉት 12 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ማጠናቂቂያ መርሐ-ግብሩ ተካሂዷል።

በመድረኩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)÷ ሰልጣኞች የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና የሆነችውን የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ለመደገፍ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው÷ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ሰልጣኞች የላቀ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ይህ ሥልጠና የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ አካላትም ምስጋና ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 እንዲሁም 46ኛው የህብረቱ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የካቲት 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.