የአጭር፣ መካከለኛ ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የሜዳ ተግባራት እና የእርምጃ ውድድሮች በዚህ ወር ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ ፣ 3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ የሜዳ ተግባራት እና የእርምጃ ውድድሮች ከታሕሣሥ 22 እስከ 26 እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ ።
በውድድሩ 21 ክለቦች፣ ሁለት ማሰልጠኛ ተቋማት እና አንድ አካዳሚን ጨምሮ 24 ተቋማት ይካፈላሉ ።
በአጠቃላይ በውድድሩ 331 ሴቶች እና 416 ወንዶች አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡
የውድድር ዕድል ብሎም ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እና በሽልማት ማበረታታትን ዓላማው ያደረገ ውድድር መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡
በዚህ ውድድር በሴቶቹ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ ወርቅነሽ መለሰ፣ አክሱማዊት አምባዬ፣ ሳሮን በርሄ፣ ነፃነት ታደሰ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡
በወንዶቹ ደግሞ አትሌት ታደሰ ለሚ፣ ጌትነት ዋለ፣ አብርሃም ስሜ፣ ሳሙኤል ፍሬው፣ መዝገቡ ስሜ፣ መለስ ንብረት እና አድሐና ካህሳይ ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል ናቸው።
በወርቅነህ ጋሻሁን