Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ወለጋ ዞን በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው የተከሰተው በተለምዶ ሲኖ ትራክ በሚል የሚታወቅ የጭነት ተሸከርካሪ እና የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ በመጋጨታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአደጋው የ11 ሰዎች ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ 12 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት መድረሱን የሲቡ ሲሬ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር ፈዮ ቡሊ ገልጸዋል፡፡

በገላና ተስፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.