Fana: At a Speed of Life!

የመሰረታዊ ባሕረኞች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ግንባታን እስከ መጋቢት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ በ16 ሔክታር ላይ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው የመሰረታዊ ባሕረኞች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ግንባታ 71 በመቶ ተጠናቅቋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል መሐመድ አሰን (ኢ/ር) እንዳሉት÷ ከ14 በላይ ሕንጻዎች ያካተተው የትምህርት ቤቱ ግንባታ የመምህራንና የተማሪዎች መኖሪያ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ፣ መዝናኛ ክበብን ጨምሮ ሌሎች ለመማር ማስተማር አስፈላጊ ሁኔታዎችን ያሟላ ነው፡፡

ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመዋኛ ገንዳና ሁለገብ ስፖርታዊ ውድድሮች ማዘውተሪያ ሜዳ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የመሰረታዊ ባሕረኞች ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ግንባታ በአማካይ ከ1 ሺህ 500 ለሚልቁ ሠራተኞች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.