Fana: At a Speed of Life!

ማኅበራዊ ችግሮች የምንፈታበት አንዱ መንገድ የበጎ ፈቃድ ሥራ ነው – አቶ መሀመድ እድሪስ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራችንን ማኅበራዊ ችግሮች የምንፈታበት አንዱ መንገድ የበጎ ፈቃድ ሥራ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ገለጹ።

በሀገራዊ አንድነት፣ በዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የሰላም ሚኒስትሩ እንደተናገሩት÷ የበጎ ፈቃድ ተግባር ብዙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች አሉት።

የበጎ ፈቃድ ተግባር በስፋት ሊሠራ የሚገባ እና እንደ ሀገርም ባህል ሆኖ መቀጠል ያለበት መሆኑን ጠቅሰው፤ የሀገራችንን ማኅበራዊ ችግሮች የምንፈታበት አንዱ መንገድ ሰው በራሱ ፈቅዶ በሚሠራ ሥራ ነው ብለዋል።

በመድረኩ እስካሁን ለተከናወኑ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎቶች ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዕውቅና መሰጠቱን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.