በሞሮኮ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ የ69 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስጠሟ 25 የማሊ ዜጎችን ጨምሮ ቢያንስ 69 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
መዳረሻቸው ስፔን አድርገው በጀልባዋ ሲጓዙ የነበሩት ስደተኞች ቁጥር 80 እንደነበር የማሊ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
ዘጠኝ የማሊ ዜግነት ያላቸውን ጨምሮ 11 ሰዎች በህይወት መትረፋቸውንም ገልጸዋል።
ከስፔን የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በፈረንጆቹ 2024 ብቻ ከ10 ሺህ በላይ አፍሪካዊያን ባህር አቋርጠው ወደ ስፔን ለመግባት በሚያደርጉት ጥረት ህይወታቸውን አጥተዋል።
ይህም በአማካኝ በቀን 30 ሰው በባህር ላይ ህይወቱ እንደሚያልፍ ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡