ኢትዮ ቴሌኮም በ67 ከተሞች የ4ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በ67 ከተሞች ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችለውን ዘመናዊ የ4ጂ LTE የሞባይል አገልግሎት አስጀመረ፡፡
የ4 ጂ LTE ኔትወርክ ማስፋፊያው በከተሞቹ በማደግ ላይ የሚገኘውን የደንበኞቹን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑን ተቋሙ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
በቀጣይም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የቴሌኮም ኔትወርክ እና ዲጂታል መሠረተ-ልማቶችን ማስፋፋቱን እንደሚቀጥል አረጋጧል፡፡