ከትጋት ውጭ የሚበለጽግ ሀገር የለም – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከትጋት ውጭ የሚበለጽግ ሀገር የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷አሁን ላይ የሥራ ባህላችን እየተለወጠ መጥቷል ብለዋል፡፡
በምሽት የተመለከቱት የሻይ ችግኝ ዝግጅት ሥራ ይበል የሚያስብል እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
ከትጋት ውጭ የሚበለጽግ ሀገር እንደሌለም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡