በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ሥድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በዚህም መሠረት 11 ከ30 ላይ ሌስተር ሲቲ በሜዳው የአምናውን ሻምፒየን ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡
እንዲሁም በተመሳሳይ ምሽት 12 ሠዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከሳውዝ ሃምፕተን፣ ኤቨርተን ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ፉልሃም ከበርንማውዝ እንዲሁም ቶተንሃም ሆትስፐር ከዎልቭስ ይጫወታሉ።
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ምሽት 2 ሠዓት ከ15 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በነገው ዕለት ደግሞ ምሽት 4 ከ45 ላይ በተመሳሳይ ሠዓት ኤፕስዊች ታውን ከቸልሲ እንዲሁም አስቶን ቪላ ከብራይተን እንደሚጫወቱ የወጣው መርሐ-ግብር ያስረዳል፡፡
በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ነገ ምሽት 5 ሠዓት ላይ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ኒውካስል ዩናይትድን ይገጥማል።