Fana: At a Speed of Life!

በጌድዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የዶራሌ ሁለገብ ወደብና ተርሚናልን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ እና ተርሚናል ተገኝቶ አጠቃላይ የገቢ-ወጪ ምርት ሂደት ጎብኝቷል።

ልዑኩ በጉብኝቱ ወቅት ከወደብ የስራ ኃላፊዎች ጋር ስለ2017/18 የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን መወያየቱን ከጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በጅቡቲ ያደረጉት ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያና ጅቡቲ ያላቸው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም ሁለቱ ሀገራት በቀጣናዊ ደህንነት፣ በንግድ፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ከጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.