Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ለ3 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አሁን ላይ ለ3 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ከሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች መካከል የተማሪዎች ምገባ አንዱ ነው፡፡

የምገባ አገልግሎቱ የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ ከመቀነስ ባለፈ ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ያለው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 9 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ቅደመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይም ከማህበረሰቡ፣ ከአጋር አካላትና ከመንግስት በተገኘ ገንዘብ ለ3 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

መንግስት ለአገልግሎቱ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው÷ለዚህም 11 ሴክተሮችን ያካተተ ስትሪግ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አገልግሎቱን በተለይም ድርቅና ሌሎች ችግሮች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.