ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን የማሕበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድማሱ ዳምጠው እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በይበልጥ አቅሙን አጠናክሮ በአዲስ መልክ መዋቀሩን በዚሁ ወቅት አቶ አድማሱ አስታውቀዋል፡፡
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም አብሮ ለመሥራት ፋናን መምረጡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው ተቋማቸው የሚሠራቸውን የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማሕበረሰብ አቀፍ ሥራዎች ለማስተዋወቅ ሰፊ አቅም ያለው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ትክክለኛው ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በፍሬው ዓለማየሁ