Fana: At a Speed of Life!

በ144 ሚሊየን ብር የተገነባው ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ማዕከል ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ሽንሌ ወረዳ በ144 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ማዕከል ተመርቆ ሥራ ጀመረ፡፡

ማዕከሉን መርቀው ሥራ ያስጀመሩት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ዑስማን ናቸው፡፡

ማዕከሉ በቀን እስከ 30 ሺህ እንቁላል የሚጥሉ ዶሮዎችን የማርባት አቅም እንዳለው እና ለ21 ሰዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.