Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን የወታደራዊ መኮንኖች የጅምላ መቃብር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ሱዳን የወታደራዊ መኮንኖች የጅምላ መቃብር ማግኘቷን አስታወቀች፡፡

የጅምላ መቃብሩ በፈረንጆቹ 1990 የተገደሉ የጦር መኮንኖች የተቀበሩበት መሆኑንም የሱዳን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡

የጦር መኮንኖቹ በሃገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አል በሽር ላይ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት በማድረግ የተሳተፉ እንደነበሩም የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መግለጫ ያስረዳል፡፡

እንደ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መግለጫ ከሆነ በጅምላ መቃብሩ 28 የቀድሞ የጦር መኮንኖች አስከሬን ተገኝቷል፡፡

በፈረንጆቹ 1989 በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት የሃገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልበሽር ከአንድ አመት በኋላ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎባቸዋል፡፡

በወቅቱም በመፈንቅለ መንግስቱ የተሳተፉ አካላትን መግደላቸው ይነገራል፡፡

አሁን ላይ በእስር ቤት የሚገኙት አልበሽር ወደ ስልጣን በመጡበት መፈንቅለ መንግስትን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙም የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል ነው የተባለው፡፡

በምዕራብ ዳርፉር በተፈጸመ የጦር ወንጀል እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ደግሞ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰዋል፡፡

አልበሽር ሱዳንን ለ30 አመታት ከመሩ በኋላ ባለፈው አመት በተነሳ ህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን መውረዳቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.