Fana: At a Speed of Life!

የሕግ ታራሚዎች የተሳተፉበት ሰደድ እሳት የማጥፋት ሥራ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአሜሪካዋ ግዛት ካሊፎርኒያ ጫካ ተነስቶ እስከ ሎስ አንጀለስ ከተማ የዘለቀው ሰደድ እሳት እስከ አሁን የ11 ሰዎችን ሕይዎት መቅጠፉ ተሰምቷል፡፡

ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት እያስተጓጎለ ያለው ከፍተኛ ነፋስም እሳቱ እንዲዛመትና እንዲስፋፋ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ሰደድ እሳቱ ከሆሊውድ መንደሯ ሎስ አንጀለስ አልፎ ወደ ሌሎች አካባቢዎች የመዛመት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

እሳቱን ለማጥፋት በሚደረገው ርብርብም ከመደበኛ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በተጨማሪ 1 ሺህ የሚጠጉ የሕግ ታራሚዎች እየተሳተፉ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ታራሚዎቹ እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ ክፍያ እንደሚፈጸምላቸው እና ይህም በካሊፎርኒያ የእርምት እና የመልሶ ማቋቋም መምሪያ (ሲሲአር) የሚመራ የረዥም ጊዜ የበጎ ፈቃድ መርሐ-ግብር አካል መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡

እስከ አሁን ከ10 ሺህ በላይ ሕንጻዎችን ያወደመው ሰደድ እሳቱ÷ በ37 ሺህ ሔክታር ላይም ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.