በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን አልፏል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን መብለጡ ተገለፀ፡፡
በሃገሪቱ አሁን ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4 ሚሊየን 170 ሺህ 333 መድረሱ ነው የተገለፀው፡፡
አሜሪካ ከዓለም በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ ስትሆን 147 ሺህ 333 ሰዎችም በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
1 ሚሊየን 979 ሺህ 617 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ሲችሉ 19 ሺህ 155 ሰዎች ደግሞ በፀና ታመው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ነው የተባለው፡፡
ከአሜሪካ በመቀጠልም ብራዚል፣ ህንድ እና ሩሲያ ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡
በብራዚል 2 ሚሊየን 289 ሺህ 952 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 84 ሺህ 207 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በህንድ ደግሞ 1 ሚሊየን 290 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 30 ሺህ 657 ዜጎቿን በሞት አጥታለች፡፡
እንዲሁም በሩሲያ ከ800 ሺህ 849 ሰዎች በላይ በቫይረሱ ሲያዙ 13 ሺህ 46 የሚሆኑት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
እንደ ወርልድ ኦ ሜትር መረጃ በአፍሪካ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን 408 ሺህ 52 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 6 ሺህ 93 የሚሆኑት ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
በዓለም ደግሞ እስከ አሁን 15 ሚሊየን 685 ሺህ 94 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 637 ሺህ 231 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
9 ሚሊየን 569 ሺህ 377 የሚሆኑት ደግሞ ማገገም ችለዋል ነው የተባለው፡፡