Fana: At a Speed of Life!

2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ሥራዎች በተያዘላቸው እቅድ እየተከናወኑ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛ ዙር የተጀመሩ ሥምንት የኮሪደር ልማት ሥራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ በ2ኛ ዙር የተጀመሩ ስምንት የኮሪደር ልማት ስራዎችን አፈፃፀም ከማለዳ ጀምረው ተዘዋውረው መገምገማቸውን አንስተዋል፡፡

የተጎበኙ አብዛኛዎቹ የኮሪደር ልማት ሥራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

ሥራው በተያዘለት እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ ጥረት ላደረጉ የከተማዋ ነዋሪዎች “ተባብረን ከተማ እየገነባን በመሆኑ ሁላችሁም የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ” ብለዋል ።

ለዚህም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.