Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ቴሌኮም በአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትልቅ እምርታ እያሳየ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ቁልፍ ተዋናይ በመሆን ትልቅ እምርታ እያሳየ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ አስታወቁ።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሰለሞን ኩዋይኖር፣ የባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ሪጅን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሊያንድር ባሶሌ (ዶ/ር) እና የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር ቡድን ኢትዮ-ቴሌኮምን በጎበኘበት ወቅት ከዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬ ሕይወት ታምሩ ጋር ተወያይቷል።

ውይይቱ ኢትዮ-ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በሚያደርገው ትልቅ ጉዞ ላይ ያተኮረ እንደነበር ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በውይይቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፥ ኢትዮጵያ ለጀመረችው ወደተሟላ የቴክኖሎጂ ትስስር እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢኮኖሚ ግንባታ ሽግግርን በማፋጠን ለአፍሪካ ሰፊ ዲጂታል እድገት ጉልህ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ከአፍሪካ ትልቁ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች አንዱ እንደመሆኑ መጠን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ክፍተትን ለማጥበብ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን ለመፍጠርና አካታች እና ቀጣይነት ያለው እድገትን ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየተጋ እንደሚገኝም አንስተዋል።

ይህንን ራዕይ ከግብ ለማድረስ ድጋፍ ሰጪዎችን ጨምሮ ቁልፍ አጋሮችን በመሳብ የበለጸገች ዲጂታል አፍሪካን ህልም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬ ሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.