ኧርሊንግ ሃላንድ በማንቸስተር ሲቲ እስከ 2034 የሚያቆየውን ኮንትራት ፈረመ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቸስተር ሲቲው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ በቡድኑ እስከ 2034 የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ተገለጸ።
የ24 ዓመቱ ኖርዌያዊ አጥቂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአቋም መውረድ ማሳየቱን ተከትሎ ቡድኑን ሊለቅ ይችላል የሚል ጭምጭምታ ሲሰማ እንደነበር ዘገባዎች ያመላክታሉ።
ሃላንድ በፈረንጆቹ ሰኔ 2022 ነበር በ60 ሚሊየን ዩሮ የዝውውር ዋጋ ከቦሩሲያ ዶርትሞንድ ወደ ማንቸስተር ሲቲ የውል ማፍረሻው ዋጋውና ሌሎች ዝርዝር የስምምነቱ ጉዳዮች በተመለከተ መረጃ እንዳላገኘ ፉትቦል ትራንስፈር የተባለ ድረገፅ ዘግቧል።
ሃላንድ በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጋቸው 87 ጨዋታዎች 79 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን÷ ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችና አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማሸነፉ ይታወሳል።