Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ለማሳደግ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በቻይና ምክር ቤት የልማት ምርምር ማዕከል ፕሬዚዳንት ሉ ሃኦ የተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ቻይና የንግድ ግንኙነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ምክክር ማድረጋቸውን ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ጠንካራ የንግድ ግንኙነት መኖሩን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ወደፊት የላቀ ትብብር ማድረግ የምንችልባቸውን መስኮች ለይተን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

በተለይም ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ማሳደግና የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተጨማሪ መስኮችን የዳሰሰ ውጤታማ ውይይት መደረጉንም አንስተዋል፡፡

ልዑኩ በጥራት መንደር ባደረገው ጉብኝት ኢትዮጵያ ለጥራት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይተናል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.