Fana: At a Speed of Life!

የከተራና የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጥር 10 እስከ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የ2017 ዓ.ም የከተራና የጥምቀት በዓል በድምቀት እንዲከበር በጥምር የፀጥታ አካላቱ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱ ተገልጿል፡፡

ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ጥምቀተ ባህር ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በ500 ሜትር ክልል ውስጥ ታቦታት ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም በሚሄዱባቸው መንገዶች ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

እንዲሁም ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት በአካባቢው የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፦
– ከ6 ኪሎ አደባባይ – ምኒልክ ሆስፒታል
– ከምኒልክ ሆስፒታል – መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
– ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ – 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም
አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
– ከዋልያ ቢራ – ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
– ከአቃቂ ዋናው መንገድ – ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
– ከ08 – አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ስለሚሆን አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባቸው ገልጾ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.