ኢትዮጵያና ኢራን ኢኮኖሚያዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኢራን አቻቸው ቫሂድ ጃላልዛዴህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ÷ ኢትዮጵያና ኢራን በኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም በግብርና፣ በማዕድን፣በማኑፋክቸሪንግና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር መስራት የሚችሉበት እድል መኖሩን ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር የጋራ የኢኮኖሚ ኮሚሽን በማቋቋም ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በደቡብ ለደቡብ ትብብር ማዕቀፍ የጋራ ግንኙታቸውን ለማጠናከር ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡