Fana: At a Speed of Life!

በኢራን አፈ-ጉባኤ የተመራው ልዑክ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የሚያጠናክር ቆይታ ማድረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራን ሪፐብሊክ መንግስት ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ (ዶ/ር) የተመራው ልዑክ በኢትዮጵያ በነበረው የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ቆይታ ማድረጉ ተገለጸ።

ልዑኩን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ተገኝተው ሸኝተዋል።

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያና በኢራን ምክር ቤቶች መካከል የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እና የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል።

የኢራን ምክር ቤት የልዑክ ቡድን በቆይታው በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጉን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.